የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለ ስልጣን “የተቋሙን ስኬቶች ለማስቀጠል የህብረተሰቡ ድርሻ የላቀ ነው በሚል መሪ ቃል” ከተማ አቀፍ የህዝብ ንቅናቄ አድርጓል።
በንቅናቄ መርሀ ግብሩም የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የባለ ስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸውና አቶ ከፍ ያለው ታደሰ እንዲሁም የ11ዱም ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በተደረገው የህዝብ ንቅናቄ መድረክም የ2018 ዓ/ም የስራ አፈጻጽም ሪፖርት ቀርቧል። የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለ ስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የስራ አፈጻጽም በከተማዋ የሚስተዋሉ 9ኙ የደንብ ጥሰቶቾን አስቀድሞ ከመከላከል ጀምሮ እርምጃ በመውሰድ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት 81.3 % መቀነሳቸውን ገልጸዋል።
ተቀናጅተው ከሚሰሯቸው ባለ ድርሻ አካላት መካከል የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሆኑን ጠቁመው በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶችን ለመከላከል በሚያከናውኗቸው ተግባራት ፖሊስ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ እና የተገኘው ውጤት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይመምሪያ ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም በበኩላቸው በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶችን አስቀድሞ ከመከላከል ጀምሮ ጥቆማ በመስጠት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልጸዋል።



