በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደረገለት

Written by

in

በአሜሪካ ኦሪገን በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደረገለት፡፡

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 2 ወርቅ፣ 3 ብር እና 1 ነሐስ በድምሩ 6 ሜዳልያዎችን በማግኘት ውድድሯን አጠናቃለች።

የዘንድሮውን ውድድር አዘጋጇ አሜሪካ 24 ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ በበላይነት አጠናቃለች።

ኬንያ በ11 ሜዳልያ 2ኛ ሆናለች ፤ ኢትዮጵያ ከዓለም 5ኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን አጠናቃለች።

ከሁለት ዓመት በፊት በፔሩ ሊማ በተደረገው ተመሳሳይ ውድድር ኢትዮጵያ 6 የወርቅ ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ሜዳልያ በማግኘት ማጠናቀቋ ይታወሳል።

ሻምፒዮናው በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ዩጂን ከተማ ሄይዋርድ ፊልድ ከሐምሌ 29 ቀን እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ተካሂዷል፡፡

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *